Etiópia

lAND.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2026-08-05 05:30:35
በኢትዮጵያ ከ36 በመቶ በላይ የሚሸፍን የደን መሬት ለግብርና ሥራ መዋሉን፣ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በቀረበ ጽሑፍ ተመላከተ፡፡ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በተካሄደው ‹አፍሪካ ኢቪደንስ› የተሰኘ ጉባዔ ላይ የፖሊሲ ጥናት ማዕከል የጥናት ባለሙያ ሮቤል ሰይፈ ሚካኤል ያቀረቡት ጽሑፍ እንደሚያስረዳው፣ በአገሪቱ የእርሻ መሬት መስፋት አሳሳቢ ችግር መሆኑንና እየጨመረ የመጣ የሕዝብ ቁጥር የፈጠረው የምግብ ፍላጎት ማሻቀብ ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህም ምክንያት አርሶ አደሮች ለእርሻ የሚሆን መሬት ፍለጋ ደን እንዲያመናምኑ እያደረጋቸው ነው ይላል፡፡ ተመራማሪው አገሪቱን ዋጋ እያስከፈላት ያለ ችግር በሚል የገለጹት ይህ ድርጊት፣ ለእርሻ ለልማት የሚውል መሬት ፍለጋና የግብርና ሥራ መስፋፋት ቀዳሚው የደን መመናመንና መመንጠር ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ አርሶ አደሮች በደን ምንጣሮ የሚሳተፉት ምርት ለማምረትና ገቢ ለማግኘት አስበው ቢሆንም፣ ውጤቱ ሲታይ ግን የአርሶ አደሮች ሕይወት ሲለውጥ አለመታየቱን ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. 2019 ጀምሮ ባለፉት ሰባት ዓመታት በቀጠለው ‹‹አረንጓዴ አሻራ›› በመባል በሚታወቀው የመንግሥት መርሐ ግብር ወደ 48 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ዓመታዊ ፕሮግራም በዚህ ዓመትም ቀጥሏል፡፡  መንግሥት ይህን ዓመታዊ የችግኝ ተከላ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአገሪቱ የደን...
pOLITICS-22.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2026-08-05 05:29:34
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለሚያደርጉ የውጭ ዜጎች የሚሰጥ የአሥር ሺሕ ዶላር ቪዛ ከመጪው ዓመት ጀምሮ እንደሚሰጥ ገለጸ፡፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት ለማድረግ ለሚፈልጉ የውጭ ዜጎች የሚሆንና ለአሥር ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ያዘጋጀው ወርቃማ ቪዛ፣ በ2019 ዓ.ም. መጀመሪያ መስጠት እንደሚጀምርና ቪዛውን ማግኘት የሚፈልግ የውጭ አገር ኢንቨስተር አሥር ሺሕ ዶላር መክፈል እንደሚጠበቅበት፣ የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምቦ መቃሳ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹አሥር ሺሕ ዶላር ሲባል ትልቅ ገንዘብ ይመስለናል፤›› ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ነገር ግን ከኢሚግሬሽን አሠራሮችና ቪዛው ለውጭ ኢንቨስተሮች ከሚሰጠው ጥቅም አኳያ መታየት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ መንግሥት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እየሠራቸው የሚገኙ ሥራዎች አካል መሆኑን፣ ኢንቨስት ለማድረግ ወደ አገር ውስጥ በመግባት የመኖሪያ ጊዜ ፈቃዳቸው የተጠናቀቀ የውጭ አገር ዜጎች ሲያቀርቧቸው የነበሩ ቅሬታዎችን የሚፈታ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ቪዛውን ማግኘት የሚችሉ ኢንቨስተሮች ከአሥር ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ሊኖራቸው እንደሚገባ፣ ሆኖም የአምስት ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት  ኖሯቸው የተሰማሩበት የኢንቨስትመንት ዘርፍ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር ሊያስገኝ የሚችል ከሆነ ቪዛውን ማግኘት ይችላሉ ብለዋል፡፡ አገልግሎቱ ቪዛውን እንዲያቀርብ የፈቀደው ደንብ በሚኒስትሮች...
Translate »