Etiópia

Awash.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2024-10-10 05:21:27
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የዛሬ 30 ዓመት በቀዳሚነት ወደ ገበያ በመግባት የሚጠቀሱት አዋሽ ባንክና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከግል የፋይናንስ ተቋማት ገበያውን በመምራት እየተጓዙ መሆናቸውን ገለጹ፡፡ ሁለቱ እህትማማች የፋይናንስ ተቋማት የተመሠረቱበትን 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ እንዳስታወቁት፣ በኢንዱስትሪው በየዘርፋቸው በገበያው ውስጥ በመሪነት ደረጃ የሚያስቀምጣቸውን አፈጻጸም ማስቀጠላቸውን አመልክተዋል፡፡ የፋይናንስ ተቋማቱን የ30 ዓመታት ጉዞ በተመለከተ የሁለቱም ተቋማት ሥራ አስፈጻሚዎች ትናንት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ በገበያ ውስጥ የያዙት ድርሻ እየሰፋ መምጣቱንም ጠቁመዋል፡፡ የ30 ዓመታት ጉዞ በተመለከተ የአዋሽ ባንክ ሥራ አስፈጻሚው አቶ ፀሐይ ሽፈራው አክለው እንደገለጹትም፣ ‹‹ቀድመው ወደ ባንክና ኢንሹራንስ ክፍለ ኢኮኖሚው በመግባት የመጀመሪያዎቹ የሆኑት እህት ኩባንያዎቹ፣ በዘርፉ ላለፉት 30 ዓመታት አገልግሎታቸውን ከወቅቱ ጋር እያዘመኑ በመሄድ ከፍተኛ ተከታታይነት ያለው ዕድገት አስመዝግበዋል፤›› ብለዋል፡፡ የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጂባት ዓለምነህም፣ ኩባንያቸው ከግል መድን ሰጪዎች መካከል በጄኔራል ኢንሹራንስ ዘርፍ ተከታታይ ዓመታት የመሪነት ደረጃውን አስጠብቆ በመጓዝ ሲሆን፣ በሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ ደግሞ ከአጠቃላይ ኢንዱስትሪው ግንባር ቀደም ሆኖ የአንደኛነትን ደረጃውን ይዞ መቀጠሉንም አመላክተዋል፡፡ እህት...
Buissines.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2024-10-10 05:19:18
ከዓለም ሕዝብ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው በመድኃኒት ዋጋ ከፍተኛ መሆን የተነሳ ችግር ላይ እንደሚወድቅ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየናረ ከመጣው የመድኃኒት ዋጋ አንጻር በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶችን ማኅበረሰቡ ቢጠቀም ተመራጭ ነው የሚል ምክረ ሐሳብ በተደጋጋሚ ሲሰነዘር ይደመጣል፡፡ ምንም እንኳን መንግሥት በአገር ውስጥ የሚመረቱ የመድኃኒቶች ውጤቶች በኅብረተሰቡ እንዲለመዱና የገበያ ድርሻቸውም ከፍ እንዲል ቢፈልግም፣ ነገር ግን ሒደቱ በአገሪቱ ላይ በቂ የጥራት ቁጥጥርና ፍተሻ የሚደረግባቸው ማዕከላት ባለመኖራቸው የቁጥጥር ከባቢውን ጎዶሎ እንዳደረገው፣ ይህም የጥራት ደረጃቸው የተረጋገጡ በአገር ውስጥ የተመረቱ የመድኃኒት ውጤቶች በበቂ ሁኔታ ለገበያ እንዳይቀርቡ እንቅፋት ስለመሆኑ የሚናገሩም አሉ፡፡  የኢትዮጵያ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አምራቾች ማኅበር 21ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ በኢሊሌ ሆቴል ባካሄደበት ወቅት የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አምራች ዘርፉን ለማሳደግ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ዕውቅና ከመስጠት ባሻገር ማኅበሩ አሁናዊ ያላቸውን ችግሮች መነሻ በማድረግ በቀጣይ አምስት ዓመታት በስትራቴጂካዊ ዕቅድ መመለስ የሚገባቸውን ጉዳዮች የተመለከተ የዳሳሰ ጥናት ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ማኅበር የቦርድ አባልና የአፍሪ ኪዩር መድኃኒት መሥራችና ባለቤት ታደሰ መኮንን  (ዶ/ር)፣...
Sahile-2.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2024-10-09 18:41:44
ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም. የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ፀድቆ ከጥቂት ወራት በኋላ ነሐሴ 15 ቀን 1987 ደግሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በማድረግ፣ የመጀመሪያውን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን (ዶ/ር) በፕሬዚዳንትነት መምረጣቸው አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ከፕሬዚዳንታዊ ሹመቱ ጀምሮ፣ ለስድስት ዓመታት ያሳለፉትን የሥራ ሕይወት እስከ ስንብታቸው ድረስ ‹‹የነጋሶ መንገድ›› በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ነፍስኄር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ነጋሶ (ዶ/ር) በዝርዝር ተርከውት ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ቦሌ የሚገኘው ቤታቸው አቶ ኩማ ደመቅሳ ለአስቸኳይ ስብሰባ እንደጠሯቸው ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) ይጠቅሳሉ፡፡ እንደ ሀሰን ዓሊና አባዱላ ገመዳን የመሳሰሉ የወቅቱ አንጋፋ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) አመራሮች ባሉበት በተደረገው ስብሰባም፣ ነጋሶ (ዶ/ር) ለርዕሰ ብሔርነት ሥልጣን መታጨታቸው እንደተነገራቸው ያስታውሳሉ፡፡ ገና የ51 ዓመት ጎልማሳ መሆናቸውንና ለክልልም፣ ለአገርም ሆነ ለፓርቲያቸው ጠንካራ የፖለቲካ  ሥራ መሥራት የሚችሉበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በመጠቆም፣ ለፕሬዚዳንትነቱ ሌላ አንጋፋ ሰው እንዲፈለግ በመግለጽ ዕጩ ላለመሆን መከራከራቸውን ነጋሶ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የኦሕዴድ አመራሮች ከእሳቸው የተሻለ በዕድሜ፣ በዕውቀትና በልምድ የበሰለ ሰው እንደሌለ በመጥቀስ እንዳሳመኗቸው፣ ይጠቅሳሉ፡፡ ፓርቲው...
kibur-ministerrr.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2024-10-09 18:40:24
ዛሬ አነዳድህ አላማረኝም። ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር? አነዳድህ አላማረኝም! የሆንከው ነገር አለ? ጤንነት እየተሰማኝ አይደለም ክቡር ሚኒስትር። እስኪ ዳር ያዝና አቁመው። እሺ ክቡር ሚኒስትር… ይኸው። ምን ሆነሃል? ምን ያልሆንኩት አለ ብለው ነው ክቡር ሚኒስትር። እንዴት ምንድነው የሆንከው? ግፊት አለብኝ። ስኳሬም ጨምሯል… ኩላሊቴንም ይሰማኛል። መቼ ነው የጀመረህ? ከለውጡ ወዲህ ነው። እንዴ… ስድስት ዓመት ሙሉ ደብቀኸኝ እያስታመምክ ነው የቆየኸው? ኧረ እንደዚያ አይደለም ክቡር ሚኒስትር። እና መቼ ነው የጀመረህ? በዚህ ሳምንት ነው የጀመረኝ። ቅድም ከለውጡ ወዲህ ነው አላልክም እንዴ? አዎ፣ ብያለሁ። ምንድነው የምታወራው? ክቡር ሚኒስትር ከለውጡ ወዲህ ነው የጀመረኝ እያልክዎት ነው። የትኛው ለውጥ? የምንዛሪው። ምን? የውጭ ምንዛሪ ለውጡ። እ…? ከዚያ ወዲህ ነው የጀመረኝ። [ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው] ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ፡፡ ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን ብር ነው ያዋጣሁት።  ይህንን እንኳን...
Ethiopian-Reporter-social-media.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2024-10-09 08:43:45
. . . ያዲሱ ትውልዳችን አስተሳሰብና ዝንባሌ እጅግ ደርቆ የገረረም ባይሆን፣ እርጥብ አይደለም፡፡ እንደ ዓባይ ያሉ የዓለሙ ቤተ ውኃዎች፣ ቀስ በቀስ የሞት አፍንጫ እያሸተቱ (ውኃቸው እያነሰ) እንደመጡ፣ ግንዛቤ አለው፡፡ በኤፍራጥስና በጤግሮስ ጭን ሥር ተሞላቃ ያደገችው ባቢሎን፣ በሥልጣኔ አብባ እንደ ነበር፣ ከታሪክ አንብቧል፡፡ የውኃ ማሕፀኖች ሥልጣኔን ሊወልዱ እንደሚችሉ ጠርጥሯል፡፡ ታድያንን የራሱ ዓባይ ዥረት ዝንተ ዓለም እየዘፈነና እያቅራራ፣ ደንኑና አረሁን ጥሶ ወደ ቆላ ሲወርድ ዝም ብሎ ማየት የሚዋጥለት አይሆንም፡፡ ስለሆነም ‹‹መላ-በሉ›› ማለቱ አልቀረም፡፡ የ‹‹እናስቀረው-ያጣላል››ም ዚቅ፣ ሳይገባው አልቀረም፡፡ ‹‹ሰላም እንዳይኖረን›› ካረጉን ምክንያቶችም አንዱ ነው ይል ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ፣ ‹‹አገር ያፈራውን ሲሳይ፣ የአገሩ ዜጋ የማይጠቀምበት ከሆነ፣ የአገር ሕዝብነት ትርጉም ምንድን ነው?›› ብሎም ይጠይቅ ይሆናል፡፡ ‹‹ውኃችን አፈር ይዞ እንዳይሄድ ወንፊት ይዤ ልቅረብም›› ይል ይሆናል፡፡ . . . ‹‹የምድሪቱን ፀጋ፣ ውኃን ሆነ ዓየራት፣ ሣር ቅጠሉን ሳይቀር፣ ማዕድን እፀዋት፣ መጠቀም እንድችል፣ በጋራ በኅብረት፣ ኧረ ሰዎች በሉ፣ ድረስ ነፊ ወንፊት፣ አገሩ ተዝቆ፣ ተንዶ ሳይሸፍት፣ ዶማና አካፋ፣ ያ ዓባይ ሆኖበት፣ እንደቡልዶዘርም፣ ነድሎ ገፎ ወስዶት፣ ራቁቱን ሳይቀር፣ ዓባይ ተወን በሉት!...
Ethiopian-Reporter-social-media.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2024-10-09 08:41:10
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia ‹‹ብሽቅ!›› ኤደንብራ ውስጥ የሚገኙ የዊቨርሊ ደረጃዎች ነፋስ ይበዛባቸዋል፡፡ ከዓመት ዓመት ያለማቋረጥ ኃይለኛ ነፋስ እንደነፈሰ ነው፡፡ ታዲያ አንድ ቀን አንዷ ሴት ወይዘሮ ባቡር ልትሳፈር ተቻኩላ ደረጃዎቹን እየሮጠች ወጥታ ስትጨርስ ነፋሱ ገለባት፡፡ ተናዳ ያያት ሰው መኖሩን ለማወቅ ዞር ብላ ስትመለከት አንዱ ከታች ያጮልቃል፡፡       ‹‹ወደ ሥራህ ብትሄድ አይሻልህም?!››አለችው በተግሳጽ፡፡       ‹‹እሺ፣ እሄዳለሁ፤ ግን ትላንትም የለበሽው ይህንኑ የውስጥ ሱሪ ነበር አይደል?›› አላት፡፡ አረፈዓይኔ ሐጐስ ‹‹የስኮትላንዳውያን ቀልዶች›› (2005) The post ‹‹ብሽቅ!›› first appear on ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by አንባቢ Source link
EYAPA-3.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2024-10-07 23:42:50
ምክር ቤቱ ፓርቲዎች ያቀረቡት ጥያቄ በቃል ኪዳን ሰነዱ መሠረት አይደለም ሲል ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣቱና የሥራ ዘመኑ ከተጠናቀቀ ከወር በላይ ያስቆጠረ መሆኑ ታምኖ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጋራ ምክር ቤቱን አባል ፓርቲዎች በአስቸኳይ ጉባዔ እንዲጠራ አምስት ፓርቲዎች ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ምርጫ ቦርድ አስቸኳይ ጉባዔ እንዲጠራ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ ኅብረ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኅብር ኢትዮጵያ)፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዋብን) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ናቸው፡፡ ፓርቲዎች ዓርብ መስከረም 24 ቀን 217 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት የአቋም መግለጫ፣ የጋራ ምክር ቤቱ አመራር የሥራ ዘመኑ ከተጠናቀቀ ከወር በላይ ስላስቆጠረ ከዚህ በኋላ ስብሰባ መጥራት አይችልም ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ የጋራ ምክር ቤቱን አባል ፓርቲዎች በአስቸኳይ ጉባዔ በመጥራት፣ ለቀጣይ አመራር ምርጫና አጀንዳ ቀረፃ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ጠይቀዋል፡፡ ቦርዱ በፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሠራርና በፓርቲዎች መካከል ያለው የጋራ ጉዳያቸውን በመተማመን መንፈስ የማስፈጸም ፍላጎት የሚጎዳ ተግባርና አካሄድ ጣልቃ በመግባት ማስቆም አለበት ሲሉ፣ ፓርቲዎች...
Editorial-1.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2024-10-07 23:41:49
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን የሁለቱም የምክር ቤት አባላትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ሹማምንት፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ንግግር በይፋ ይጀመራል፡፡ በፕሬዚዳንቷ የመክፈቻ ንግግር ያለፈውን የመንግሥት  አፈጻጸምና የዘንድሮን ዕቅድ አስመልክቶ መሠረታዊ ጉዳዮች እንደሚነሱ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያን አስጨንቀው የያዙ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጣቸው ይታመናል፡፡ ፋታ የማይሰጡና አጣዳፊ መፍትሔ የሚሹ በርካታ ችግሮች ባሉባት ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ለዋና ዋና ብሔራዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት ዘለቄታዊ ሰላም ለማስፈንና የአገር ህልውናን ለማስቀጠል የሚበጅ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ ዓምና ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሦስተኛ የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ ‹‹…ምንጊዜም ቢሆን ለሰላምና ለንግግር የሚረፍድ ጊዜ የለም…›› በማለት መንግሥት ከማንኛውም ኃይል ጋር ችግሮችን በመወያየትና በንግግር የመፍታት ቁርጠኝነት እንዳለው፣ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም መቋጨቱን በዋቢነት መጥቀሳቸው ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን አስጨንቀው ከያዟት ዋነኛ ችግሮች መካከል ተጠቃሹ፣ በየቦታው የሚስተዋለው የፀጥታ መደፍረስ ነው፡፡...
Finanace.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2024-10-07 15:06:59
የዋጋ ንረትን ተከትሎ የኑሮ ውድነት ተባባሰ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የመኖር ሕልውና አደጋ ላይ ወደቀ፣ እየተባለ ሲነገርባቸው የነበሩት ያለፉት ዓመታት ዛሬ ላይ ተደራርቦ ከመጣው የመንግሥት  ተቋማት  የአገልግሎትና ዋጋ ጭማሪ ጋር ሲታይ ምንም አልነበሩም የሚባልበት ወቅት ላይ ደርሰናል ይላሉ፣ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ነዋሪዎችና ሰርክ የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የሚከታተሉ ባለሙያዎች፡፡ መንግሥት በቅርቡ ይፋ ካደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ገበያው መሽቶ በነጋ ቁጥር በተለያየ ጭማሪዎች እየተጨናነቀ ባለበት ሁኔታ፣ የተለያዩ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተናበቡ ይመስል እያደረጓቸው ያሉ የዋጋ ጭማሪዎች፣ ‹‹መንግሥት ሕዝቡ ላይ እልሁን እየተወጣ ነው ወይ?›› የሚል ጥያቄ የጫረባቸውም አልጠፉም፡፡ በተለይም አብዛኛው ማኅበረሰብ የኢኮኖሚ ጫናውን ይጠብቅ የነበረው ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች  ወይም ከግሉ ዘርፍ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ቢሆንም፣ በዚህ ወቅት እየታየ ያለው በግልባጩ ከመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መሆኑ መነጋገሪያ አድርጎታል፡፡ የመንግሥት የአገልግሎት ክፍያዎች በከፍተኛና ፈጣን በሆነ ሁኔታ ዜጎች ላይ መጫኑ አሳሳቢነቱን የሚያስረዱት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች በኢትዮ ቴሌኮም፣ በንግድ ባንኮች፣ በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን፣ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣንና በመሳሰሉት መንግሥት አገልግሎት የሚሰጥባቸውና...
Untitled.png
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2024-10-07 15:05:32
እስከ ዛሬ ድረስ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ የነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢፌዲኤሪ ፕሬዝዳንት በመሆን ሳህለወርቅ ዘውዴን ተክተው ተሾሙ። ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ አምባሳደር ታዬ ያለምንም ተቃውሞ፤ በአምስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ሹመቱ ጸድቆላቸው በምክር ቤቱ ፊትለፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለአዲሱ ተሻሚ አምባሳደር ታዬ ህገ መንግስቱን በማስረከብ ኃላፊነታቸውን አስረክበው በክብር ተሰናብተዋል። Source link
plugins premium WordPress
Translate »