Etiópia

photo_2026-08-08_09-03-59-e1786169204499.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2026-08-08 09:14:10
ትናንት ከምሽቱ 11:42 ሰዓት በኦሪገን በተካሄደው የሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊያኑ ወጣቶች ተከታትለው በመግባት የወርቅና ብር ሜዳሊያ አጥልቀዋል። አትሌት አልማዝ ዮሐንስ ርቀቱን 9:15:81 ሰዓት አጠናቃ አንደኛ ሆና የፈጸመች ሲሆን ፤ የገባችበች ሰዓትም የውድድሩ ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦላታል። ወሰኔ አሰፋ ደግሞ በ9:30: 50 ሰዓት ሁለተኛ ሆና የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች፤ የራሷን የአመቱን ምርጥ ሰአትም አስመዝግባለች። ሻምፒዮናው ዛሬ ቅዳሜ በአኛ ቀን ውሎው ይቀጥልና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበት ሶስት የፍፃሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ፤ ከሰዓት በኋላ ከ11:10 ጀምሮ በወንዶች 5000 ሜትር የእርምጃ ውድድር ነገሮ አዱኛ፥ ምሽት11:17 ሰዓት ደግሞ በሴቶች 800 ሜትር ፍፃሜ ደራርቱ ሽብሩና ሀብታም ገበየሁ፣ እንዲሁም 11:53 ሰዓት ላይ በሴቶች 3000 ሜትር ሽቶ ጉሚና ዮርዳኖስ ፅጋብ ለፍፃሜ ይሮጣሉ። እስካሁን ኢትዮጵያ አንድ ወርቅ በአልማዝ ዮሐንስ፣ በ3000 ሜትር ሴቶች መሰናክል፥ ሁለት ብር በወሰኔ አሰፋ 3000 ሜትር መሰናክልና በሴቶች 5000 በሽቶ ጉሚ እንዲሁም አንድ ነሀስ በ5000 ሜትር ወንዶች በዳምጠው ከበደ የተገኘ ሲሆን፣ በጥቅሉ አራት ሜዳሊያዎች ማግኘት ተችሏል። Source link
IMG_20260808_113613_918-e1786178257781.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2026-08-08 09:13:07
የግራንድ አፍሪካ ረን ” ከሩጫም በላይ ነው!” በሚል መርሃ ግብር እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ፣ በአሜሪካና በሌሎች የአፍሪካ አገራት ድጋፍ የሚሹ ማኅበረሰቦችን ከሚያገለግሉ አስር ተቋማት ጋር በቅንጅት ሊሰራ ነው። አጋር ድርጅቶቹ በካንሰር ግንዛቤና ሕሙማን ድጋፍ፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ወገኖችን በማገዝ፣ የሕፃናት ትምህርትን በመደገፍ፣ ድህነትን በመቀነስ፣ የነርሶችና የሌሎች ባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት እንዲሁም ንጹሕ የመጠጥ ውኃ በማቅረብ ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውን ገልጿል። የድርጅቱ ተወካዮች ማኅበረሰቡ እ.አ.አ ኦክቶበር 10 ቀን 2026 በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ በሚደረገው አፍሪካን ግራንድ ረን ዝግጅት ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችም የመረጡትን የበጎ አድራጎት ድርጅት በመደገፍ ተሳትፏቸውን ትርጉም ያለው እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የሩጫ ውድድሩ ዓላማ በሚመለከት እንደተገለጸው፣ በምዕራቡ ዓለም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሩጫ ዝግጅቶችን ለገቢ ማሰባሰቢያነት ይጠቀሙበታል። በተመሳሳይ መልኩ እነዚህ 10 ድርጅቶች ግራንድ አፍሪካ ራንን እንደ መድረክ በመጠቀም፣ ተሳታፊዎች ከወዳጅ ዘመዶቻቸውና ከሥራ ባልደረቦቻቸው ገቢ እንዲያሰባስቡ ዕድል ያመቻቻሉ። ተሳታፊዎች የአምስት ኪሎ ሜትር ርቀቱን በመክፈል ወዳጆቻቸው ለእያንዳንዱ ርቀት ድጋፍ እንዲያደርጉ በኢሜይል፣ በአጭር ጽሑፍ፣ በስልክ ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ መጠየቅ ይችላሉ። የሚሰበሰበው ገቢ በቀጥታ ወደ ተመረጠው ድርጅት የሚገባ ሲሆን፣...
photo_2025-05-10_16-36-51.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2026-08-06 14:28:14
አንተ የት ጠፍተህ ከርመህ ነው ዛሬ የደወልክልኝ? ጋሼ ሰሞኑን ድንገት ጦርነት ተቀሰቀሰ ሲባል ሰምቼ ነው የደወልኩልህ፡፡ የሰሞኑ እኮ ትንሽ ጦሽ ጦሽ እንጂ ያን ያህል ጦርነት የሚባል አልነበረም፡፡ ወሬው እኮ በአንዴ ዓለምን ነው ያዳረሰው ጋሼ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ወሬ ዓለምን በአንዴ እንደሚያዳርስ የታወቀ ነው፡፡ ጋሼ በቃ አገራችን ሁሌም ከጦርነት ጋር ብቻ ነው እንዴ ስሟ የሚነሳው? አስደናቂው ልማታችን እኮ ትኩረት እየተነፈገው እንጂ እጅግ በጣም የሚያኮራ ነው፡፡ ጋሼ ሁሌም አገራችን ችግር ላይ ሆና አንተ ግን ስለአስደናቂ ልማታችሁ ማውራት ነው የሚቀናህ፡፡ እናንተ ግማሽ ቀን የተደረገ ለአቅመ ጦርነት የማይበቃ ጦሽ ጦሽ ላይ ስትከርሙ እኛ እዚህ ታሪክ ሠርተናል፡፡ ኧረ ጋሼ አታስቀኝ እባክህ፣ ደግሞ ምን ዓይነት ታሪክ ሠራችሁ? አልሰማሁም እንዳትለኝ ብቻ? ጋሼ አንተው ንገረኝ እንጂ አንተ ሠራን የምትለውን ታሪክ ፈፅሞ አልሰማሁም፡፡ እኔ በበኩሌ አልፈርድብህም፣ ልብህም ሆነ ጆሮህ ያለው የማይረባ ወሬ ላይ ነው፡፡ ጋሼ ዓለም እየተቀባበለ ያወራውን ጦርነት ለምን ሰማህ እያልከኝ ነው? እኔ አልወጣኝም፣ ግን ልማታችንንም በዚህ መጠን ብትከታተል የምልህ ይገባህ ነበር፡፡ እኔ ያልሰማሁትን፣ እናንተ ደግሞ የሠራችሁትን ታሪክ ለምን...
photo_2026-08-06_16-42-08-e1786023774294.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2026-08-06 14:26:55
በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት አውዳሚ ጦርነት በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲቆም፣ ሁሉም እግዚአብሔርን በቅን ልቡናና በትሑት ሰብእና እንዲጠይቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ጥሪ አቀረቡ።ቅዱስ ፓትርያርኩ አባታዊ ጥሪያቸውን ያቀረቡት ነገ ነሐሴ 1 ቀን  የሚጀመረውን የ2018 ዓ.ም. የፍልሰታ ለማርያም ጾምን አስመልክተው ለመላው የእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፉት መልእክት ነው።የፍጥረት አውዳሚ ጦርነት እንዲቆም ምእመኑ ፈጣሪን እንዲጠይቅ ያሳሰቡት ቅዱስ ፓትርያርኩ በመልእክታቸው፣ ባልንጀራ ማለት የተወሰነ የማኅበረሰብ ወገን ሳይሆን መላውን የሰው ወገን እንደሚያካትት ገልጸው፣ ፍቅርና መከባበር በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ሊኖር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተውበታል።ምእመናን በአሥራ አምስቱ ቀን የሱባዔ ጊዜ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተግባራት በማከናወን፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ፣ የተራቡትን በመመገብና የታረዙትን በማልበስና የተጣሉትን በማስታረቅ እንዲያሳልፉ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ Source link
Social-88.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2026-08-06 06:18:56
የጤና ተቋማት የሚመረጡበትና የጤና ምርመራ ሒደታቸውን በተመለከተ ዝርዝር የአፈጻጸም መመርያ አይወጣም ወደ ባህረ ሰላጤ አገሮች ለሥራ ለሚሄዱ ዜጎች የሚደረግ የሕክምና ምርመራን የሚያስተባብረውና የሚያቀርበው ‹‹ዋፊድ›› የተባለው የሕክምና ምርመራ ፕሮግራም፣ ግልጽ ማስታወቂያ ሳይወጣና ከጤና ሚኒስቴር ዕውቅና ውጪ በሆነ አሠራር የጤና ተቋማትን የሥራ ብቃት ለመመዘን ምዝገባ እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የሰባት አገሮች ጥምረት በሆነው የባህረ ሰላጤው አገሮች የጤና ካውንስል (Gulf Health Council) ሥር የሚገኘው ዋፊድ (WAFID) ፕሮግራም፣ ወደ ሰባቱ አገሮች ለሥራ የሚሄዱ ዜጎችን የጤና ምርመራ የሚያደርጉ የጤና ተቋማት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የምዘና ሒደቱን የሚያካሂድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለምዘናው ፍላጎት ያላቸውን የጤና ተቋማት በፕሮግራሙ በተዘጋጀው የበይነ መረብ ሥርዓት (Online System) በመጠቀም ምዝገባ የሚያካሂድ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ምዝገባውን ለማካሄድ ፍላጎት ላላቸው ተቋማት ግልጽ ማስታወቂያ በማውጣት የሚገለጽ ቢሆንም፣ ሥርዓቱ ከተዘረጋባቸው አዲስ አበባ፣ አዳማና ጅማ ከተሞች ውስጥ በአዳማና በጅማ ከተሞች ግልጽ ማስታወቂያ ሳይወጣና ከጤና ሚኒስቴር ዕውቅና ውጪ የግል የጤና ተቋማት ምዘናውን ለማከናወን በኦንላይን ምዝገባ አካሂደው ውጤት እየተጠበቀ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአዳማና በጅማ ከተሞች ከግንቦት 3 እስከ 6...
IMG_20260806_094625_884.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2026-08-06 06:16:52
– “የዘመሙ አካሄዶች ሲታዩ በጊዜውና በወቅቱ ዕርምት ይደረግባቸዋል” የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን – 250ው ስልታዊ ቡድን አዲስ አበባና ድሬዳዋ የፌዴራል አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል የአገራዊ የምክክር ጉባዔ በአጀንዳ ጭብጦች ላይ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ የተመደቡ አመካካሪዎች፣ምሁራንና ቃለ ጉባዔ ያዦች፣ ተመካካሪዎች የሚያነሱትን ሃሳብ ባለመቀበልና በተለይ የመጡበትን ተቋም መሠረት ያደረገ አቋም በመያዝ፣ ተመካካሪዎች ሐሳብ እንዲቀይሩና የምክክር ሒደቱ እንዲዘገይ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተመካካሪዎች ገለጹ በተለይ መንግሥትን ወክለው የመጡ  አመካካሪዎች እንደ የመንግሥት አደረጃጀትና አገር ግንባታ ያሉ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከምክክሩ ሒደት ባፈነገጠ መልኩ የራሳቸውን ሐሳብ ማንፀባረቃቸውን ምንጮች ተናግረዋል። የመንግሥት አደረጃደት አጀንዳን በተመለከተ እንዲያወያዩ በኮሚሽኑ የተመደቡ አመካካሪዎች በዚህ የተነሳ ለቀናቶች ውይይት እንዳይመሩና ማይክ ብቻ እንዲያቀብሉ በማድረግ፣ በእነርሱ ምትክ ደግሞ ከቡድን መሪዎች ተመርጠው ውይይት እንዲመሩ መደረጉን ገልጸዋል። ከዚህ አልፎ የኮሚሽኑ አመካካሪዎች ውይይት እንዲመሩ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩን ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ የአጀንዳ ሐሳብ በተለይ የተለያዩ የፓርቲዎችን ወክለው  የተገኙ ተመካካሪዎች የአመካካሪዎች አካሄድ በተመለከተ ቅሬታ አቅርበው ሁኔታው ከላይ በተገለጸው መንገድ እንዲመራ መደረጉን ተመካካሪዎቹ ተናግረዋል። From The...
cARTOON-1.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2026-08-05 21:58:34
ሰሞኑን በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል የአንድ ቀን ድንገተኛ ውጊያ መካሄዱ ተሰምቷል፡፡ በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት ወታደራዊ ኃይሎች መካከል ተደረገ የተባለው ውጊያ፣ እንደ ከዚህ ቀደሙ የሁለት ዓመታት አውዳሚ ጦርነት አድማሱ ከሰፋ ሊከተል የሚችለው ዕልቂትና ውድመት ብዙዎችን ሥጋት ውስጥ ከቷል፡፡ በኢትዮጵያ ከአራት ሺሕ በላይ ተሳታፊዎች የታደሙበት አገራዊ የምክክር ጉባዔ እየተካሄደ ባለበት ወቅት፣ በሌላ በኩል በአገር ላይ ትልቅ ችግር ሊያስከትል የሚችል የጦርነት ነጋሪት ሲጎሰም ከሥጋት ባለፈም ከፍተኛ ፍርኃት ይፈጠራል፡፡ ከዚህ ቀደም በተደረጉ ጦርነቶችም ሆነ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ሥፍራዎች በሚካሄዱ ውጊያዎች፣ እየተጎዳ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ከግጭቶች በመለስ ተቀምጦ በሥርዓት ለመነጋገር የሚያስችል ፍላጎት በመጥፋቱ ብቻ፣ አገር እየደማችና እየቆሰለች ህልውናዋ ለአደጋ ከመጋለጧ ባሻገር ሕዝቡም ሕይወቱ ለከፋ ችግር እየተዳረገ ነው፡፡ ጦርነት ግን በአገር ላይ የተጋረጡ ችግሮችን እንደማይፈታ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ጦርነትም ሆነ የጦርነት ወሬ እንዳንገሸገሸው፣ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በግልጽ ሲናገር በተደጋጋሚ ተደምጧል፡፡ በከፍተኛ የኑሮ ጫና ውስጥ ሆኖ ከከፋው ድህነት ለመገላገል የሚያስችሉ የልማት ዕቅዶች የሚያስፈልጉት ሕዝባችን፣ ከጦርነት አባዜ እንዲላቀቅ መፍትሔ ካልተፈለገለት የራሱም ሆነ...
FAYDA.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2026-08-05 21:56:51
­ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) አገራዊ የዲጂታል ሕዝባዊ መሠረተ ልማትን ለማጠናከር ‹‹ፋይዳቨርስ ዲጂታል ሶሉሽንስ ኢንተርፕራይዝ›› በሚል ስያሜ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ እንደገና መቋቋሙን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አስታወቀ፡፡ በፕሮጀክት ደረጃ ሲንቀሳቀስ የነበረው ፋይዳ ይፋዊ አገራዊ ግልጋሎት በሚሰጥ ፋይዳቨርስ (Faydaverse) በተሰኘ የመንግሥት የልማት ድርጅት ደረጃ ተደራጅቶ በይፋ መቋቋሙ፣ ትናንት ማክሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ ተደርጓል። ፋይዳቨርስ ዜጎችን፣ ንግዶችንና ተቋማትን የሚደግፍ አስተማማኝ የዲጂታል ሕዝባዊ መሠረተ ልማት (DPI) መፍትሔዎችን የመገንባት፣ የማንቀሳቀስና የማስፋፋት ኃላፊነት እንደተሰጠው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ተቋሙ የአገሪቱን ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ሀብቶች የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) አካል ሆኖ መቀላቀሉም ተገልጿል። ይህ ሞዴል ተቋሙ አቅሙን እንዲያሰፋ፣ አጋርነቶችን እንዲያጠናክር፣ ኢንቨስትመንትን እንዲስብና ከኢትዮጵያ አገራዊ የልማት ግቦች ጋር የተጣጣሙ የዲጂታል መፍትሔዎችን ማልማቱን እንዲቀጥል እንደሚያስችለው በመግለጫው ተነግሯል፡፡ ፋይዳቨርስ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መስክ ያላትን ሚና እንደሚያጠናክር፣ አገሪቱ በትልቅ ደረጃ የዲጂታል ማንነት መሠረተ ልማትን በመተግበር ረገድ ያላትን ልምድ በመጠቀም በመላው አፍሪካ የዕውቀት ልውውጥን፣ የቴክኒክ አጋርነቶችንና የዲጂታል ሕዝባዊ መሠረተ...
Anti-coruption.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2026-08-05 13:44:35
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን አስመልክቶ ያለውን ግንዛቤ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፣ የመሬትና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ መሆኑን አረጋግጫለሁ አለ፡፡ የመሬት አስተዳደርና የይዞታ ምዝገባ፣ የገቢዎችና ታክስ ጽሕፈት ቤቶች፣ የኮንስትራክሽን ፈቃድ ቁጥጥር፣ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮች በከፍተኛ ደረጃ ለሙስና ተጋላጭ መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል ብሏል፡፡ ኮሚሽኑ ለዳሰሳ ጥናት በተወሰደ ናሙና ከ60 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሙስና በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ተግባራት ከፍተኛ እንቅፋትና ችግር የፈጠረ አሳሳቢ ችግር መሆኑን እንደነገሩት ገልጿል፡፡ በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት፣ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ውስብስብና ግልጽ ያልሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደቶችና የሕግ ማስከበር ድክመቶች ለሙስና መስፋፋት ዋነኛውንና ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ የጥናት ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በጥናቱ ጉቦ ለመስጠት የሚገደዱ ሰዎች ለድርጊታቸው የሚያቀርቡት አንዱ ምክንያት አገልግሎቱን ለማግኘት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ግለሰቦች ጉቦ የሚሰጡት የሚፈልጉት አገልግሎት እንዲፈጸምላቸውና የሚጠበቅባቸውን ባለማድረጋቸው ሊደርስባቸው የሚችለውን እንግልት ለማስቀረት መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡ የሙስና ድርጊትን ለመጠቆም የሚፈልጉ ግለሰቦች ሊደርስባቸው የሚችል የበቀል ዕርምጃና የማስፈራራት ሥጋት በመኖሩ፣ አስተማማኝ የጠቋሚዎች ጥበቃ ሥርዓት ማነስ፣ እንዲሁም የጥቆማ አሰጣጥ...
Moges.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2026-08-05 13:43:18
እ.ኤ.አ. በ2025 ዕዳው ወደ 122 ቢሊዮን ብር ማሻቀቡ በገለልተኛ ኦዲተሮች ይፋ ተደርጎ የነበረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ በ2018 በጀት ዓመት ለዘመናት ከተከማቸበት ዕዳ ወጥቶ 39.5 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን፣ 2018 በጀት ዓመት ተቋሙ ለዓመታት ከተከማቸበት ዕዳ ወጥቶ ወደ ትርፍ የተሸጋገረበት ዓመት እንደነበርም ለሪፖርተር ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኦዲት ሰርቪስ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የተፈራረሙበትና በገለልተኛ ኦዲተሮች ተከናውኖ እ.ኤ.አ. በየካቲት 2026 የወጣው ሰነድ ኪሳራው እ.ኤ.አ. በ2025 122 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቆ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ሆኖም አቶ ሞገስ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተቋሙ ለዓመታት ከነበረበት ኪሳራ ወጥቶ ወደ ትርፍ የተሸጋገረበትንና ያልተጣራ 39.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ያስመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል። ለተደጋጋሚ ጊዜ ይቀርብ የነበረውን የተቋሙ ከፍተኛ ዕዳ መንግሥት መሸከሙ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱ፣ የአገሪቱን የኃይል ማመንጨት አቅም እጥፍ በሚባል ደረጃ መጨመሩና የዳታ ማይኒንግ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ መጀመራቸው ለተገኘው ውጤት ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። ኤሌክትሪክ ኃይል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...
Translate »