Etiópia

Untitled-1-16.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2024-12-18 01:50:46
ለጤናማ የግብይት ሥርዓት እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው የሚታመኑ በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ በገበያ ውስጥ የምርት እጥረት እንዲፈጠርና የዋጋ ንረትን የሚያባብሱ ናቸው ብለን ከምንጠቅሳቸው ውስጥ ምርት በመሸሸግና ጊዜ ጠብቆ ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት አንዱ ነው፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድ፣ የደላሎች ጣልቃ ገብነትና የመሳሰሉ ሁኔታዎች ለገበያ ያለመረጋጋት ምክንያት ስለመሆናቸው በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ነው፡፡ የብር የመግዛት አቅም መዳከምና ሌሎች ለዋጋ ንረት ምክንያት ናቸው የሚባሉ ሰው ሠራሽ ውንብድናዎችም ችግሩን በማባባስ የየራሳቸው አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አደናቃፊ ሁኔታዎችም የግብይት ሥርዓቱን በማደነቃቀፍ በገበያው ውስጥ የሚያስከትሉትን ተፅዕኖዎች በተግባር እያየን ነው፡፡ የሰላም ዕጦት አልፎ ለዋጋ ንረት ይዳርጋል፡፡ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎችን ያዳክማል የንግዱን ኅብረተሰብ ሠርቶ የመኖር መብት ይነካል ለሸማቾች መድረስ የሚገባው ምርት በወቅቱ እንዳይደርስ፣ ከዚያም አልፎ ለዋጋ ንረት ይዳርጋል፡፡ እዚህ አካባቢ የፀጥታ ችግር አለ በሚል ወሬ ብቻ ተንቀሳቅሶ ለመሥራት ሥጋት ያላቸው አካላት የሚደርስባቸው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሌላው የችግሩ አካል ነው፡፡ እስካሁን ከምንሰማቸው ሕገወጥ ተግባራትና የተለመዱ ተግዳሮቶች ባሻገር ሕገወጥ የተባሉ ኬላዎች እየተፈጸሙ ነው የተባለው ችግር ደግሞ በግብይት ሥርዓቱ ውስጥ አዲስ ተግዳሮት ሆኖ...
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2024-12-18 01:49:41
(ክፍል ሁለት) በታደሰ ሻንቆ የትግልና የኑሮ ተሞክሮዎች ያነጠሩልን ሐሰተኛ ግንዛቤዎች የሰው ልጅ ኑሮ በጉርብጥብጥና በሸለቆ በተሞላበት እውነታ ውስጥ ነፃነትና ሰንሰለቶች ጉራማይሌ ህልውና አላቸው፡፡ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ሥነ ምግባር፣ ርዕዮተ ዓለም፣ እምነት፣ ወዘተ ከኅብረተሰብ ወደ ግለሰብ፣ ከግለሰብ ወደ ኅብረተሰብና ከግለሰብ ወደ ግለሰብ ሲተላለፉ እንደኖሩ ሁሉ የሰንሰለቶች ቀለበቶችም እንደዚያ ይሸጋገራሉ፡፡ ከዚህ በፊት እንደተባለው ለህሊና ሰንሰለቶች መተላለፊያ ሠረገላቸው ብዙ ነው፡፡ መደበኛና ኢመደበኛ ትምህርት፣ ሥነ ቃል፣ ሙዚቃ፣ እምነት፣ ወዘተ ሁሉ ሠረገላ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዛሬ በፈጣሪና በመላዕክት እንደሚማለው የአፄ ኃይለ ሥላሴ ስምም መማያ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ የኃይለ ሥላሴ ውዳሴ በእነዚህ በእነዚህ መንገዶች ናኘ ወይም ወደ ሕዝብ ሠረፀ ብሎ ለመዘርዘር ከመሞከር ይልቅ፣ ለዘመኑ ኅብረተሰብ በጡጦ መሰጠት የቀረው ምግብ ነበር ብሎ መናገር ይቀላል፡፡ ትችትን ያነወረ ውዳሴን መቅለብ፣ ምን ያህል በሰንሰለት መያዝ እንደሆነ ወይም ምን ያህል እንደሚገንዝና የለውጥ ተቀናቃኞች መጫወቻ ለመሆን እንደሚዳርግ ትናንትናም ታይቷል፣ ዛሬም እያየነው ነው፡፡ ልሂቃን የፖለቲካ ፓርቲዎች ፈጥረውም ሆነ ሳይፈጥሩ ተራማጅ ነን/ለሕዝብ ተቆርቋሪዎች ነን እያሉ ሲንቀሳቀሱ ለሕዝብ ህሊና ብርሃን ሊሆኑ እንደሚችሉ ሁሉ በሰንሰለት ተብታቢዎችም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡...
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2024-12-17 17:33:54
(ክፍል አንድ) በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) መንደርደሪያ ለኢትዮጵያ፣ ለበርካታ ዘመናት፣ የመሬት ባለቤትነት፣ ይዞታ፣ ውርስ፣ አጠቃቀም የመብትና ተዛማጅ ጉዳዮች ለአገር ደኅንነት ሆነ ለሉዓላዊነቷ ተከብሮ መቆየት የነበራቸው አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም፡፡ ዛሬም ሆነ ወደፊት በመርህ ደረጃ እነዚህ ጉዳዮች የሚኖራቸው መሰል ሚና ጉልህና አዎንታዊ ነው፡፡ የመሬቱ ባለቤት ከሆነ ዜጋው ለአገሩ ሲባል የማይከፍለው ዓይነት መስዋዕትነት የለም፡፡ በአጠቃላይ በመሬት ባለቤትነት፣ ልማትና አጠቃቀም ዙሪያ እስከ ዛሬ የነበሩ የሕዝብ አስተዳደር ሥርዓቶችና ፖሊሲዎች ለአገሪቷ ብልፅግና፣ ለሕዝቡ ማኅበራዊ ዕድገት ይዘትና ደረጃ የወሳኝነት ሚና እንደነበራቸው በርካታ የታሪክ ጸሐፍት ሰንደውት ይገኛል፡፡ ለምሳሌ እነ ፓንክረስትና ክሬሚ ከ55 ዓመት በፊት በጻፏቸው መጻሕፍት ውስጥ መሬትና ከመሬት ጋር የተያያዙ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ዜጎች ያፈሯቸው ተጓዳኝ ንብረቶችና ተያያዥ የነበሩ ኋላ ቀር የአጠቃቀምና የምርት ክንዋኔዎችና ግንኙነቶች፣ ለግብርናው ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢኮኖሚ፣ ውስብስብ ችግር ፈጣሪ ሆነው ለዘመናት መቆየታቸውን በመረጃና ማስረጃ ላይ ተመርኩዘው ሰንደውታል፡፡ እነሱ እስከ አፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ጊዜ ድረስ ባለው መረጃ የደረሱበት ድምዳሜ ከዚያም በኋላ ባሉት መንግሥታት፣ እስከ ዛሬም ድረስ፣ ሳይቀየር ሊነገር በሚችልበት ይዘት ላይ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ...
Social-22.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2024-12-17 17:32:39
በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት ጥሎ ያለፈው መከራ ሳያባራ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት፣ በኦሮሚያ ያለው የሰላም ዕጦትና በሌሎች አካባቢዎች መለስ ቀለስ እያለ የሚታየው ግጭት ለአገሪቱም ሆነ ለነዋሪዎቿ ፈተና ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕዝቦች ለችግር ተጋልጠዋል፡፡ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ተፈናቅለዋል፡፡ ሴቶት ለጥቃት ተጋልጠዋል፡፡ በሰላም ከአንዱ ሥፍራ ወደ ሌላው መንቀሳቀስ ፈተናና ሥጋት ሆኗል፡፡ ተምኪን ይሃ፣ ፋሀሌን አብዱራህማን፣ ቢንያም ሃፍቶም ግጭቶች በሰላም ይፈቱ ዘንድ የተጀመሩ ሥራዎች ቢኖሩም፣ በቅጡ መሬት አልረገጡም፡፡ ስለሆነም ብዙኃኑ ሰላም ይሆንለት ዘንድ በየፊናው ይታትራል፡፡ በሰላም ዕጦት ከተፈተኑት ከትግራይ፣ ከአማራና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የመጡት ታዳጊዎችም ሰላም ስለመጠማታቸው ይገልጽልናል ያሉትን ሥዕል በመያዝ በየክልላቸው ሰላም እንዲሰፍንና ዘላቂነቱ እንዲረጋገጥ ጠይቀዋል፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ በፈገግታ ተሞልታ የምትማር ተማሪን በሥዕል ሥራዋ ይዛ የቀረበችው የአማራ ክልል የሕፃናት ፓርላማ አፈ ጉባዔ ተምኪን ይሃ፣ ሰላም ከሰው ፊት ገጽታ የሚነበብ፣ ከአኗኗሩ የሚታይ ነው ትላለች፡፡ የተማሪዎች ክፍል ውስጥ መገኘት ሰላምን የሚገልጽ ቢሆንም፣ በክልሉ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ልጆች ከትምህርት እንደራቁ፣ የኢኮኖሚ ችግር እንደገጠማቸውና ሴቶች ፆታዊ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነም ትገልጻለች፡፡ ‹‹ከተማሪዎች ፊት...
plugins premium WordPress
Translate »