Etiópia

Social-33.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2025-01-22 00:08:27
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ የመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ጫና በኢትዮጵያ ግብርናና የአመጋገብ ሥርዓት ላይ አደጋ ደቅኗል ተባለ፡፡ ይህ የተነገረው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የምግብና ሥርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ላይ ትኩረቱን ያደረገ ኮንፈረንስ፣ ከጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ፍኖተ ካርታ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መመዘኛ ሲታይ በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉና በንጥረ ነገር የበለፀጉ ምግቦች፣ የምግብ ደኅንነት ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሠረተ ልማቶችና የአልሚ ምግብ እጥረት ከፍተኛ ውስንነት መኖሩ ተገልጿል፡፡ የግብርናው ዘርፍ 65 በመቶ የሥራ ዕድል፣ 72 በመቶ የወጪ ንግድ ገቢ፣ 32 በመቶ ጥቅል አገራዊ ምርት እንደሚሸፍን የገለጹት የግብርና ትንራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ባለሙያው አቶ መሠረት ፀጋዬ ናቸው፡፡ የአየር ንብረት መዛባት የሙቀት መጨመር፣ የተቆራረጠ ዝናብ፣ ጎርፍና ድርቅ የመሳሰሉ ከባድ የሆኑ የተፈጥሮ ክስተቶች፣ የዓሳ፣ የእንስሳትና የጥራጥሬ ምርት መቀነስ እያስከተሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት የዝናብ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሆኑን ጠቅሰው፣ በአንዳንድ ወራት ደግሞ የበረታ ዝናብ ለድንገተኛ ጎርፍና ለአፈር መሸርሸር እየዳረገ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2000 እስከ 2023 ድረስ በኢትዮጵያ የተከሰቱ 30...
Chamber-44.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2025-01-22 00:07:30
ከጉባዔው አንድ ቀን በፊት አባል ሆነው የተመረጡ 55 ነጋዴዎች ለቦርድ አባልነት መቅረባቸውም ግርምትን ፈጥሯል የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት መተዳደሪያ ደንብ፣ ጠቅላላ ጉባዔው ከምክር ቤቱ መደበኛ አባላት መካከል ፕሬዚዳንቱንና ምክትል ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ አሥራ አንድ የቦርድ አባላትን የመምረጥ፣ የመሾምና የመሻር ሥልጣን እንዳለው ቢገልጽም፣ በ18ኛ ጠቅላላ ጉባዔው የቀረበው የምርጫ አመቻች ኮሚቴ፣ ከየ ክፍለ ከተማው ተወክለዋል ያላቸውንና ጠቅላላ ጉባዔው ከመካሄዱ አንድ ቀን በፊት የአባልነት ፎርም እንዲሞሉ ከተደረጉት 55 ነጋዴዎች መካከል 11ን ለቦርድ አባልነት መርጦ ለጉባዔው ማቅረቡ ታወቀ። ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም. የተካሄደው የምክር ቤቱ 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የምርጫ ሒደቱን አስመልክቶ የኮሚቴው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሃጎስ ኃይለ ሚካኤል ለታዳሚዎቹ ማብራሪያ አቅርበዋል። በማብራሪያቸውም ‹‹ከአሥራ አንዱም የከተማዋ ክፍላተ ከተሞች እያንዳንዱን ክፍለ ከተማ የሚወክል አምስት አምስት ሰው በተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በተቀመጠው መሥፈርት መሠረት እንዲቀመጥ በማድረግ፣ አጠቃላይ 55 ሰዎች ውክልና አግኝተው ከምርጫ በፊት ጠርተን የአባልነት ፎርም እንዲሞሉ አድርገናል። ያንን ይዘን የሁሉም ክፍለ ከተማ ውክልና ባላቸው ሰዎች ቦርዳችንን መርጠናል፤›› ብለዋል። የዘርፍ ማኅበሩ ጥር 1...
Afar.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2025-01-21 15:46:43
የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች በሙሉ ተፈናቅለዋል ተብሏል በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን በሚገኙት በአዋሽ ፈንታሌና በዱለቻ ወረዳዎች በቀጠለው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከአካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች እየቀረበ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ድጋፍ ተጠየቀ፡፡ በዋናነት በሁለት የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙና ቁጥራቸው በየቀኑ እየጨመረ ይገኛል ለተባሉ ተፈናቃዮች፣ በፌዴራል አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽንና በክልሉ መንግሥት በተቋቋመው ድጋፍ ማስተባበሪያ ኮማንድ ፖስት በኩል አስቸኳይ ዕርዳታ እየቀረበ ነው ተብሏል፡፡ ይሁን እንጂ ቁጥሩ እየጨመረ ካለው ተረጂና አደጋው ከመቀጠሉ አንፃር ድጋፉ በቂ ባለመሆኑ፣ የሚመለከታቸው በሙሉ ተጨማሪ ድጋፍ በማቅረብ እንዲተባበር የአካባቢው ባለሥልጣናት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአሚባራ ወረዳ በሚገኘው ሲዲ አፋጊ ዳኢዶ መጠለያ፣ እንዲሁም በአዋሽ ፊንታሌ ወረዳ ባለው ኢረብሃራ (ቻይና ካምፕ) መጠለያ በርካታ ሰዎች እየገቡ መሆኑን፣ የአካባቢው ዕርዳታ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ወደ አዋሽ ከተማና ወደ አርጎባ ወረዳዎች የገቡ መኖራቸውም ተነግሯል፡፡ በአጠቃላይ ከ9,000 በላይ ቤተሰቦች ከሁለቱ አደጋ ከደረሰባቸው ወደረዳዎች መፈናቀላቸውን ነው የገለጹት፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ4,000 በላይ ሠራተኞች ያሉት የከሰም ስኳር ፋብሪካ በአደጋው ተጎድቶ ሥራ በማቆሙ፣ ሠራተኞቹ በሙሉ ተፈናቅለው ለተረጂነት መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡ ይህን...
MOF.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2025-01-21 15:37:58
የአገሪቱ የውጭ ዕዳ ጂዲፒ ጥምርታ ለደሃ አገሮች ከተቀመጠው ጣሪያ አልፏል የኢትዮጵያ ኖሚናል ጂዲፒ (የዋጋ ንረትን ታሳቢ ያላደረገ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት) በዶላር ሲተመን፣ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከነበረበት 207 ቢሊዮን ዶላር በሦስት ወራት ውስጥ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር መውረዱ ተገለጸ፡፡ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከመደረጉ አንድ ወር በፊት ማለትም በሰኔ 2016 ዓ.ም. የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በገንዘብ (በዶላር) ሲሰላ 207 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከተደረገ በኋላ በ2017 ዓ.ም. መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር መውረዱን የገንዘብ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው የሩብ ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት የዕዳ ሰነድ አስታውቋል። የአገሪቱ ጂዲፒ በዶላር ሲተመን ያሽቆለቆበት ምክንያትም ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ተግባራዊ በመደረጉ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል። በዚህና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. የአገሪቱን ጂዲፒ 32.9 በመቶ ይዞ የነበረው አጠቃላይ የመንግሥት የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ (Public Debt) በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም. ወደ 50.3 በመቶ አሻቅቧል። የመንግሥት (የአገሪቱ) የውጭ ዕዳ መጠን ለብቻው ተነጥሎ ሲታይ፣...
Health.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2025-01-21 00:53:01
በኢትዮጵያ በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተከሰቱ ጦርነቶችና ግጭቶች ምክንያት እየተስተጓጎለ የመጣውን የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መልሶ ለማጠናከር ያስችላል የተባለ የ1.28 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሴቶችን በቀጥታ እንዲሁም ከአምስት ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለውን የሥነ ተዋልዶ ጤና መረጃና አገልግሎት ፕሮጀክት በአማራ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡ በአምስት ክልሎች ለሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሥነ ተዋልዶ ጤና መረጃና አገልግሎት ተደራሽነት ለማጠናከር የታለመው ፕሮጀክት፣ ለሰባት ዓመታት የሚተገበርም ይሆናል፡፡ ባገባደድነው ሳምንት በአይፓስ ኢትዮጵያ፣ በጤና ሚኒስቴርና የገንዘብ ድጋፉን ባደረገው የካናዳ መንግስት ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ሴቶች፣ ልጃገረዶችና ማኅበረሰቡ የራሱን ጤና ለመጠበቅ በመረጃና በግንዛቤ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔ እንዲያሳልፍ የሚያስችልም ነው ተብሏል፡፡ የአይፓስ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ደመቀ ደስታ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ ፕሮጀክቱ አስፈላጊ ሀብት ከማቅረብ ባለፈም ሴቶችና ልጃገረዶች የሥነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅና አገልግሎት ፍላጎታቸው ላይ ለመወያየት ደኅንነቱ የተጠበቀ ድባብ መፈጠርንም የሚያጠናክር ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ በፋብሪካዎችና በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሠሩ ሴቶች፣ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውና በገጠር የሚኖሩ ሴቶችን ጨምሮ የሥነ ተዋልዶ...
Untitled-1-16.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2025-01-21 00:49:02
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡ አገራዊ ኢኮኖሚውን ከመደገፍና ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች የሚውል ካፒታል ለማሰባሰብ እንደ አንድ አማራጭ የሚወሰድና ለኢትዮጵያ እንደ አዲስ ምዕራፍ የሚታይ ዕርምጃ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ረዥም ዕድሜ ያለው አገር ካፒታል ገበያ ብርቅ ሆኖባት እስከዛሬ መቆየቱ አግባብ እንዳልነበር ካሰብንም ገበያው ዘግይቶም ቢሆን መጀመሩ እንደ አገር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ በሌላ አንጻር ዛሬ እንደ አዲስ ብለን የጀመርነው የካፒታል ገበያ ከዛሬ 60 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ይሠራበት የነበረ መሆኑን ስናስብ ደግሞ በመካከል የጠፋው ጊዜ ማስቆጨቱ አይቀርም፡፡ ቀድመን እንደመጀመራችን በዚያው ባለመቀጠላችን እናገኝበት የነበረው ጥቅም ምን ያህል እንደሆነም መገመት አያዳግትም፡፡  የካፒታል ገበያ በንጉሡ ጊዜ እንደ አጀማመሩ ቢቀጥል ዛሬ ሊደረስበት የነበረው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በእጅጉ የተለየ ይሆን ነበር የሚለው ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህም በኋላ በዚህ ገበያ በአግባቡ ለመጠቀም በርትቶ መሥራት ግድ ይላል፡፡ የካፒታል ገበያ መፈጠር ይዟቸው የሚመጡ በርከት ያሉ ዕድሎች ይኖራሉ፡፡ በዋናነት ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች የሚሆኑ ካፒታል መፍጠር ዋናው ነገር ነው፡፡ ዜጎችም ባላቸው አቅም በገበያው ኢንቨስት እያደረጉ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ዕድል ይሰጣል፡፡ ገንዘብ በባንክ...
Serkalem.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2025-01-20 11:34:06
የነዳጅ ግብይት ሥርዓትን ለመዘርጋትና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ አዲስ አዋጅ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡ በኢትዮጵያ በነዳጅ ሥርጭት ግብይትና በአጠቃላይ በዘርፉ ያሉትን ማነቆዎች ሊያቃልል ይችላል የተባለው ይህ አዋጅ፣ አሁንም ክፍተት እንዳለበት እየተገለጸ ነው፡፡ በፀደቀው አዋጅና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ የነዳጅ ግብይት ላይ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች መካከል አንዱ ከሆኑት ሰርካለም ገብረ ክርስቶስ (ዶ/ር) ጋር ዳዊት ታዬ ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ሪፖርተር፡- የነዳጅ ግብይትና ቁጥጥርን የተመለከተ አዋጅ ሰሞኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡ የአዋጁን ድንጋጌዎችና አስፈላጊነት እንዴት ያያሉ? ዶ/ር ሰርካለም፡- ምንም ዓይነት ነገር የሕግ ማዕቀፍ ከሌለው ለሙስና፣ ለግብይት ሥርዓት ብልሽትና ለመሳሰሉት ችግሮች ተጋላጭ ይሆናል፡፡ በየትኛውም ዘርፍ ያለ ቢዝነስ የራሱ የሆነ ሕጋዊ አሠራር ያስፈልገዋል፡፡ ከነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ሕገወጥ ተግባራት በሙሉ በሕግ ካልተያዙ ከፍተኛ ችግር ያስከትላሉ፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ የነዳጅ ግብይት ሥርዓቱን ለመቆጣጠር የሚያስችል እንዲህ ያለ አዋጅ አስፈላጊነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡ እንዲያውም ይህ አዋጅ ዘግይቷል ባይ ነኝ፡፡ በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም ከ10 እና 15 ዓመታት በፊት ከነዳጅ ግብይት...
Ethiopian-Reporter-social-media.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2025-01-20 11:33:03
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia የምድራችን (የሰው ልጆች) ተማፅኖ — አረንጓዴ ፖለቲካ! (ወጥመዶችና ማምለጫችን) በታደሰ ሻንቆ የወጥመዶች ዓለም በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ዘንድ ያሉ ውዝግቦችና ግጭቶች ምንም ተቀባቡ ምን፣ መሬትን ውኃን አፈርን ማዕድናትን ንግድንና መሰል ጥቅሞችን የተመለከቱ ናቸው፡፡ በእነዚህ ውዝግቦች ውስጥ ትናንትናን ለዛሬ ማጣቀስ እንዳለ ሁሉ፣ ‹ይህ አገር ከተመዘዘ ለጥቅሜ አይተኛምና ከወዲሁ ላዳቀው› የሚል ሁሉ ሥሌት አለ፡፡ በቅርብ ጉርብትናዎቻችን ውስጥ ልናስተውላቸው የምንችላቸው የጥቅም ፍትጊያዎችና ፀቦች፣ ሰፋ ባለ ክፍለ አኅጉራዊ ደረጃ የንዑስ ኃያላን ስብስብና ተቀናቃኝነት በተለያየ መልክ ሠርተው እናገኛቸዋለን፡፡ በአኅጉር ደረጃም እንደዚያው፡፡ አኅጉርንና አኅጉራትን በዘለለ ደረጃ ልዕለ-ኃያላን አገሮች የራሳቸውን ጎራዊ ስብስብ ሠርተውና እየሠሩ በሚፋተጉ ፍላጎቶቻቸው ዓለምን ይንጣሉ፣ ይዘውራሉ፡፡ ግጭትና ጦርነት ይለኩሳሉ፣ ያላኩሳሉ፡፡ ከኃያላን ወታደራዊ ጦርነቶች ጀርባ ያሉት የኢኮኖሚ ጦርነቶች ናቸው፡፡ በኢኮኖሚ ጦርነቶቹ ሆድ ዕቃ ውስጥ ያሉት ትንቅንቆች ደግሞ ከዓለም ገብ ጎራዎች ጋር የተያያዙ የ‹ኮርፖሬት› ኩባንያዎች ትንቅንቆች ናቸው፡፡ ወታደራዊ ጦርነቶች የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ጦርነቶች ማስፈጸሚያ ብቻ አይደሉም፡፡ ራሳቸው ጦርነቶቹ፣ የጦር መሣሪያ ኩባንያዎች መበልፀጊያ (የወታደራዊ ኢኮኖሚ) ማካበቻና ማደጊያ...
Ethiopian-Reporter-social-media.jpg
Etiópia, Ethioobserver, Inglês/Amárico
2025-01-19 21:56:38
በጌታነህ አማረ ኢትዮጵያ ማለት ታላቅ አገር ቀደምት የሰው ዘር መገኛና የሥልጣኔ ባለቤት የሆነች አገር እንደነበረች ታሪክ ሲያወሳን ይኖራል። በዚያውም ልክ ይህች ታላቅ ነበረች የምትባል አገር አሁን ላይ በድህነት፣ በጦርነት፣ በግጭትና በስደት እየተሰቃየች የምትገኝ አገር አንድ ቀን ተመልሳ ታላቅና በዓለም ላይ ስሟ ከፍ ያለና የገነነ ችግር እንደምትሆን የብዙዎች ጥባቆት ነው፡፡ ይህ እንደሚሆን ደግሞ መተማመኛ የሚሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ ዋና ዋና የሚባሉት። በተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች መሆኗ ይህም ሲባል ሰፊ የሆነ መታረስ የሚችል መሬት፣ ሰፊ የሆነ ለደን ልማት መሆን የሚችል መሬት፣ ሰፊ የማዕድን ሀብት፣ ሰፊ የውኃ ሀብት፣ ሰፊ ለቱሪስት መስህብ መሆን የሚችል የመሬት አቀማመጥ፣ ብዛት ያላቸው ጥንተ ጽሑፎች፣ ምቹና ተስማሚ የሆነ  የአየር ንብረትና ሌሎችም አማኝ፣ አዛኝ፣ መሥራት የሚችልና አትንኩኝ ባይ ሰፊ ሕዝብ፣ ይህ ሁሉ እያለ ታዲያ ዋና ችግር የሚባለው ምንድነው ሲባል? መልሱ  አንዱ ድህነትና ኋላ ቀርነት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ብዝኃነትን የማስተናገድ ችግር ነው፡፡  ስለዚህ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ምን ይደረግ? ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት ተገቢ ይሆናል።  በመጀመሪያ ድህነትን ለማጥፋት መደረግ ያለበት...
Editorial-4.jpg
Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico
2025-01-19 21:54:07
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማደግ ያለበት በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ከሚሰበሰብ ታክስ ብቻ ሳይሆን ከግብርና፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከማዕድን፣ ከአገልግሎትና ከሌሎች ሀብት አመንጪ ዘርፎች ጭምር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ ያለ ተደራራቢ ታክሶች፣ የመንግሥታዊ አገልግሎቶች ክፍያና ታሪፍ ጭማሪዎች፣ የትራፊክ ቅጣትና ሌሎች ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የታክስና የቀረጥ ገቢዎች በዜጎች ኑሮ ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ጭማሪዎች በቀጥታ የሚተላለፉት ሸማቾች ላይ ስለሆነ ፅኑ ችግር እየተፈጠረ ነው፡፡ በፀጥታ ችግር ምክንያት በበርካታ አካባቢዎች የተረጋጋ የግብርና ሥራ እየተካሄደ አይደለም፡፡ ብዙዎቹ ፋብሪካዎች ከአቅማቸው ከግማሽ በታች ሲያመርቱ በዚያው መጠን ሥራ ያቆሙም የሉም፡፡ መንግሥት ገቢ መሰብሰብ ላይ ሲያተኩር የሚሰበሰበው ገቢ በከፍተኛ የሥራ ፈጠራ፣ በምርትና በምርታማነት ላይ ካልተመሠረተ ሁሉም ነገር ቀጥ የሚልበት አጋጣሚ ሊፈጠር ስለሚችል መንግሥት ገቢውን ብቻ ሳይሆን የሕዝቡን ኑሮ ያካተተ ስትራቴጂ ይንደፍ፡፡  ከዚህ በፊት የነበሩና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ ቅደም ተከተል ያስፈልጋል፡፡ በረጅም፣ በመካከለኛና በአጭር ጊዜ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን መለየት ይገባል፡፡ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትኩረት ከሚፈልጉ ጉዳዮች መካከል ሰላም፣ የምግብ ዋስትና፣ መጠለያ፣ የሥራ ፈጠራና የመሠረተ ልማት...
plugins premium WordPress
Translate »